vacancy details
ዛሬ የካቲት 18/2014 ዓ.ም፦ ኮሌጃችን በሚደግፋቸው 3 ወረዳዎች
ዛሬ የካቲት 18/2014 ዓ.ም፦ ኮሌጃችን በሚደግፋቸው 3 ወረዳዎች (ቸሀ፣ አበሽጌና ቀቤና) እና 2 ከተማ አስተዳደሮች (ወልቂጤና እምድብር) ለሚገኙ 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ለተውጣጡ ር/መምህራን እና የሳይንስና ፈጠራ ክበባት አስተባባሪና የፈጠራ ተሰጥኦ ካላቸው ተማሪዎች በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ኢንጅነሪንግና ሂሳብ ላይ የግንዛቤ መፍጠሪያ ስልጠናና የጉብኝት ፕሮግራም ተካሂዷል። በፕሮግራሙ ላይ የኮሌጃችን ዲን በቴክኒክ ሙያ ት/ትና ስልጠና ስትራቴጂ እና በSTEM ፅንሰ-ሀሳብ ላይ የቀረቡ ሰነዶች ላይ ማብራሪያ ያቀረቡ ሲሆን በቀረቡት ሰነጆችም ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል፤ ከተሳታፊዎች በርካታ አስተያየቶች ተሰጥቷል። በመጨረሻም በኮሌጁ የሚገኙ ት/ት ክፍሎች እንዲሁም እየተሰሩ የሚገኙ ችግር ፈቺ ቴክኒዎሎጂዎች እንዲጎበኙ ተደርጓል። የፕሮግራሙ ተሳታፊዎች ባዩት ነገር መደሰታቸውን እና በቀጣይ ከኮሌጃችን ጋር በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።










