vacancy details
ዛሬ የካቲት 24/2014 ዓ.ም: በቡታጅራ ከተማ በሚገኘው #የደስታ_ጋርመንት_ፋብሪካ ጋባዥነት የኮሌጃችን ዲኖች በቦታው በመገኘት ጉብኝት አድርገዋል።
ዛሬ የካቲት 24/2014 ዓ.ም: በቡታጅራ ከተማ በሚገኘው #የደስታ_ጋርመንት_ፋብሪካ ጋባዥነት የኮሌጃችን ዲኖች በቦታው በመገኘት ጉብኝት አድርገዋል። በጉብኝቱ አጠቃላይ የፋብሪካው የስራ እንቅስቃሴ የተጎበኘ ሲሆን በድርጅቱ ስራ አስኪያጅ አማካኝነት ሰፊ ገለፃ ተደርጎላቸዋል፤ በገለፃው በአሁኑ ወቅት ሰፊ ኢንቨትመንት በመመደብ በጋርመንት ዘርፍ ሰፊ ስራ እየሰራና የስራ እድልም እየፈጠረ መሆኑን ድርጅቱ በቀጣይ ጊዜያት ሊሰራቸው ያቀዳቸው ሰፋፊ የማስፋፊያ ስራዎች እንዲሁም ይህንን ለማከናወን ተግዳሮቶች የሆኑ ነገሮች የተነሱ ሲሆን ከተግዳሮቶቹ መካከል በቂ የሰለጠነ የሰው ኃይል ያለማግኘታቸው በዚህም ምክንያት ፋብሪካው ማምረት ከሚችለው አቅም 50% ብቻ እያመረተ መሆኑ በዋናነት ተገልጿል፤ በቀጣይም ፋብሪካው ለሚያደርገው የማስፋፊያ ኢንቨስትመንት ከ2 ሺህ በላይ የሰለጠነ ባለሙያ የሚፈልግ በመሆኑ ኮሌጃች ከሌሎች የዞኑ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ጋር በመቀናጀት አሰልጥኖ ለማቅረብ እንዲሁም ፋብሪካው ባሉት ልምድ ያላቸው የውጭ ሀገራት ባለሙያዎች ለአሰልጣኞች የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን እና ለሰልጣኞች የትብብር ስልጠና ለመስጠት በአጠቃላይ ተቀናጅቶ በሚሰራበት ሂደት ዙሪያ የጋራ ስምምነት ተደርጓል።











